Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አመራሮች እና ሰራተኞች “በዘላቂ ድል ወደ ብልጽግና የድህረ ጦርነት መዛነፎችና እርምቶቹ” በሚል ርዕስ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይዮች ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡
 
የውይይት መድረኩን የመሩት አቶ ንጉሡ ጥላሁን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ እንደገለጹት ፥ አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ዓልሞና አቅዶ የከፈተው ጦርነት በኢትዮጵያዊያን የተባበረና የተቀናጀ ትግል ድል መጎናፀፍ ተችሏል።
 
በጦርነቱ ህዝባችን ከዳር እስከ ዳር ኢትዮጵያን አላስደፍርም ብሎ በመነሳቱ የጠላት እኩይ አላማና ቅስም ከመስበሩም ባሻገር ኢትዮጵያዊያን ተቀናጅተዉ የመስራት አቅማችንን ያሳየንበትም ነው ብለዋል፡፡
 
የሽብር ቡድኑ አመራሮች በጥቂት ቀናት አዲስ አበባ እንገባለን በሚል ቀቢጸ ተስፋ በርካታ የትግራይ ወጣቶችን ለጦርነት እንደማገዱም ነው የገለጹት፡፡
 
ጦርነቱ በውጭ ጋላቢዎቹ የሚደገፈውንና ኢትዮጵያን አፈርሳለው ብሎ የተነሳውን የሽብር ቡድን ድባቅ በመምታት የህዝባችንን ጠንካራ አንድነት ያስገኘ አጋጣሚ መሆኑንም አውስተዋል፡፡
 
አሁን ላይም የሽብር ቡድኑ ህወሓት በየትኛውም መስፈርት ኢትዮጵያን የማፍረስ አቅሙ እና እቅዱ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ተቀልብሷል፤ ድልም የመላው ኢትዮጵያዊያን ሆኗል ነው ያሉት።
በቀጣይ ህወሃት የሽብር ጥቃት እና መሰል ችግሮችን ከመፍጠር ባለፈ የሀገር ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ላይ እንደደረሰም ጠቁመዋል፡፡
 
በሌላ በኩል የአሸባሪው የህወሓት ፈረስ የሆነው ሸኔ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በንጹሃን ህይወትና እና ንበረት ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ለማስቆም የተቀናጀ ስራ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
 
የሽብር ቡድኖቹን ጥቃት በዘላቂነት ለማስወገድም መንግስት ከሁሉም የጸጥታ አካላት እና ከህብረተሰቡ ጋር በትብብር ይሰራል ነው ያሉት አቶ ንጉሡ፡፡
 
ሀገርን ለማዳን ጦርነቱ በኢትዮጵያዊያን ድል አድራጊነት በዘላቂነት መቋጨት ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ሚና ከፍተኛ ነበር ያሉት አቶ ንጉሱ፥ በኢትዮጵያ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በሚሰሩ ስራዎች ሁሉ የመገናኛ ብዙሃን የሚጠበቅባቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version