Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ብሄራዊ ምክክር ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ ምክክር ለተሻለ ሃገራዊ መግባባት በሚል መሪ ሀሳብ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
 
በሀገራችን ከትርክት ጀምሮ በርካታ ልዩነቶች በመኖራቸው ይህ ብሔራዊ ምክክር አስፈላጊ ነው ሲሉ በውይይቱ ላይ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን ተናግረዋል፡፡
 
በርካታ ልሂቅ ሰራሽ ልዩነቶች ያሉ በመሆኑ ከልሂቃኑ እነዚህን ልዩነቶች በማጥበብ ረገድ ብዙ ይጠበቃል ነው ያሉት።
 
ባላፈት ሃምሳ እና ስልሳ ዓመታት የተካረረ የፓለቲካ ትርክት በመኖሩ ሀገሪቱ ዘርፈ ብዙ በሆነ መንገድ ተጎድታለችም ብለዋል፡፡
 
ለዚህ ደግሞ ዋናው ምክንያት በሰለጠነ መንገድ መነጋገር ባለመቻሉ እንደሆነ አንስተው÷ ይህንን ብሔራዊ ምክክር ከዚህ አዙሪት እንደመውጫ ልንጠቀምበት ይገባል ነው ያሉት።
በሀገራችን በታሪክ፣ በህገመንግስት እና በሰንደቅ ዓለማ ዙሪያ ልዩነት በመኖሩ ብሔራዊ ውይይት ያስፈልጋል ያሉት ደግሞ ደራሲ እና መምህር ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ ናቸው፡፡
 
በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ ያሉ ሀሳቦችን ወደ ተቀራራቢ ሁኔታ ለማምጣት ብሔራዊ መግባባት ወሳኝ እንደሆነም አንስተዋል።
 
ብሔራዊ ምክክሩም አወንታዊ ውጤት እና ሰላም እንዲያመጣ ሁሉን አካታች በሆነ መንገድ ሊደረግ ይገባል ነው ያሉት::
 
በውይይቱ የፍልስፍና ምሁሩ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ፍፁማዊ ግብ፣ ግጭት ዘለቄታዊ ሰላም በሚል ፅሁፍ ያቀርባሉም ተብሏል።
 
ብሔራዊ እርቅ ለጋራ ህልም እና ህገመንግስት ማሻሻያ ሂደት የሚል ፅሁፍ በአቶ ደረጀ ደምሴ ይቀርባል።
 
በክብረወሰን ኑሩ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version