አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገ ወጥ መንገድ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች የሚያደርጉ ግለሰቦች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ የአማራ ክልል መንግስት አሳሰበ፡፡
የክልሉ መንገስት ባስተላለፈዉ መልዕክት አሸባሪው ቡድን በአማራ ክልል ላይ ባካሄደው ወረራ በክልላችን ሕዝብ እና መንግሥት ሃብት እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ዘረፋ እና ውድመት አድርሷል።
ይሁን እንጅ የወራሪውን ቡድን ዘረፋ እና ውድመት ተከትሎ ጉዳት የደረሰባቸውን የክልሉን ሕዝቦች ለማቋቋም በሚል የተለያዩ አካላት የድጋፍ ማሰባሰቢያ የሒሳብ ቁጥሮች እና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች እያሰናዱ እንደሆነ እየተመለከትን ነው ብሏል የክልሉ መንግስት ።
ነገር ግን ይህ ድርጊት ለቁጥጥር የማይመች እና ከክልሉ መንግሥት እውቅና ውጭ በመሆኑ በዚህ አይነት ድርጊት በመሳተፍ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የክልሉ መንግሥት አሳስቧል።
በቅርቡም የክልሉ መንግሥት የማቋቋሚያ ገቢ ዝግጅቶች እና የሒሳብ ቁጥሮችን የሚያሳውቅ በመሆኑ የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለሟቋቋምና ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ የክልሉ መንግስት ጥሪ አስተላልፏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!