Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የወልድያ ዩኒቨርሲቲን ስራ ለማስጀመር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህወሃት ጉዳት የደረሰበትን ወልድያ ዩኒቨርሲቲ መልሶ በማቋቋም የመማር ማስተማሩን ስራ ለማስጀመር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አበበ ግርማ ገልጹ።

ዩኒቨርሲቲው በአፍሪካ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆን ተደርጎ የተደራጀ እንደነበር የገለጹት ዶክተር አበበ÷አሸባሪው ቡድን ወረራ በፈፀመበት ወቅት ማሽኖች፣ የመብራት፣ የውሃና ሌሎችን የተቋሙን ንብረቶችን በማውደም በታሪክ የማይረሳ ጥቁር ጠባሳ የጣለ ነው ብለዋል ፡፡

በደረሰው ውድመት የተነሳ መምህራንና ተማሪዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የመማር ማስተማር ስራ እንዲቀጥሉ ጊዜያዊ መፍትሄ መሰጠቱን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲውን መልሶ ስራ ለማስጀመር መንግስትና አጋር አካላት ጠንካራ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎችም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲሰጡ ተመድበው ማገዝ ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት መደረጉን አመልክተዋል።

በዚህም እስከ የካቲት ወር 2014 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊው ማስተካከያ ተደርጎለት መልሶ በማቋቋም የመማር ማስተማር ስራውን ለማስጀመር በቅንጅት እየሰራን እንገኛለን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version