Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከ9 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለወልድያ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ የሚሆን ከ9 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አድርጓል፡፡
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በአሸባሪው የህወሓት የሽብር ቡድን ከፍተኛ የንብረት ውድመት ከደረሰባቸው መንግስታዊ ተቋማት አንደኛው ነው።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶ/ር አብርሃም ቦሻ፥ ዩኒቨርሲቲው አሸባሪው የህውሓት ቡድን በማህበራዊ ተቋማት በተለይም በትምህርት እና ጤና ተቋማት ላይ ያደረሰው ውድመት እጅግ አሳፋሪ ድርጊት መሆኑን ገልጸው፤ ውድመቱ የደረሰባቸውን ተቋማት መልሶ በማቋቋም ሁሉም አካል የድርሻውን መወጣት አለባቸው ብለዋል።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲም በዛሬው ዕለትም 94 ለመማር ማስተማር ፣ 58 ለተማሪዎች ምግብ ቤት አገልግሎት፣ 7 ለተማሪዎች መኝታ ቤት እንዲሁም 6 ለተማሪዎች ክሊኒክ አገልግሎት የሚውሉ የዓይነት ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ መሆኑን ዶ/ር አብርሃም ጠቁመው ፥ይህም በገንዘብ ሲተመን ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ መሆኑን ገልጸዋል።
በቀጣይ ጊዜያትም ተጨማሪ ቁሳቁሶችን በመግዛት የድጋፍ እና መልሶ የማቋቋም ስራው ተጠናክሮ ይቀጣላል ነው ያሉት።
በማስተዋል አሰፋ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like
Comment
Share
Exit mobile version