አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ”የኢትዮጵያን ይግዙ” ኤግዚቢሽንና ባዛር በአዲስ አበባ መቻሬ ሜዳ ተከፍቷል፡፡
ኤግዚቢሽንና ባዛሩን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በይፋ አስጀምረዋል።
የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የተለያዩ አምራች ኢንተርፕራይዞችን በማስተባበር ያሰናዳው ኤግዚቢሽንና ባዛር የሀገር ውስጥ ምርቶችን በዋናነት ያካተተ ነው።
ይህም ወደሀገራቸው የገቡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ታሳቢ በማድረግ የሀገራቸውን ምርት በስፋት እና በአንድ አካባቢ እንዲሸምቱ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።
የዳያስፖራ አባላት የሀገራቸውን ምርት በሚሄዱባቸው ሀገራት ለማስተዋወቅ እንደሚያግዝም ተገልጿል።
ኤግዚብሽንና ባዛሩ እስከ ጥር 16 የሚቆየው ሲሆን÷ የተለያዩ የቆዳ፣ የሸማ፣ የግብርና እና ሌሎች ምርቶች መካተታቸውን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

