አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲመረምር የተቋቋመው የሚኒስትሮች ግብረ-ኃይል የአብይ ኮሚቴዎችን ረቂቅ የድርጊት ዝርዝር መርሀ-ግብር ማጽደቁን የሚኒስትሮች ግብረ-ኃይል ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ታደሰ ካሳ ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት በትግራይ ክልል በተፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ላይ ምርመራ በማካሄድ ልዩ ልዩ ምክረ-ሃሳቦችን ያካተተ ሪፖርት ጥቅምት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ማውጣቱን ዶክተር ታደሰ አስታውስው፥ የኢትዮጵያ መንግስትም ሪፖርቱን በመርህ ደረጃ ተቀብሎት እንደነበርም ተናግረዋል፡፡
በመቀጠልም የትግራይ ክልልን ጨምሮ በአማራ እና በአፋር ብሄራዊ ክልሎች የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በማካተት ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የሚሰሩ የወንጀል ምርመራን፣ የክስ እና የተጎጂዎች ድጋፍ ሥራዎችን በበላይነት የሚያስተባብር የሚኒስትሮች ግብረ-ሀይል በማቋቋም እንዲሁም የሰክሬታሪያት አደረጃጀት በመፍጠር ከህዳር 20 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ሲንቀሳቀስ ቆይቷልም ብለዋል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ በሚኒስትሮች ግብረ-ሀይል ስር የተደራጁት አራት አብይ ኮሚቴዎች የሚመሩበት የድርጊት ዝርዝር ሰነድ (Action Plan) የተዘጋጀ ሲሆን፥ ግብረ-ኃይሉ ጥር 4 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ሰነዱን መርምሮ በማፅደቅ ኮሚቴዎቹ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲገቡ የተደረገ መሆኑን ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

