Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአፋር ክልል ለሚገኙ የጸጥታ ሃይሎችና ተፈናቃይ ወገኖች የ8 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ለሚገኙ የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የክልሉ ልዩ ሃይል እና ተፈናቃይ ዜጎች የተለያዩ አካላት የ8 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን 5 ሚሊየን 300 ሺህ ብር ድጋፍ በአፋር ክልል በተልእኮ ላይ ለሚገኘው ለአገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉንም የ6ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር አመራር ኮለኔል አደራጀው ሞላ ተረክበዋል።
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል በፈፀመው ጥቃት ጉዳት ለደረሰባቸው እና ለክልሉ ልዩ ሀይል የሚውል 3 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚገመት የተለያዩ የአይነት ድጋፍ አድርገዋል ።
ድጋፉን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ምክር ቤት ዋና አፈ – ጉባኤ ሙዚና አብዱቃድር ለአፋር ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አሲያ ከማል አስረክበዋል ።
አፈ-ጉባኤ አሲያ ከማል፥ ለተደረገው ድጋፍ በተጎጂዎቹ እና በክልሉ መንግስት ስም ማመስገናቸውን ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን እና ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version