አዲስ አበባ፣ታህሳስ 9፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ “የዳያስፖራው ተሳትፎ ለሀገራችን የሳይበር ደህንነት” በሚል መሪ ሀሳብ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ከዳያስፖራው ማህበረሰብ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
የሳይበር ደህንነት ጉዳይ ለአንድ ተቋም ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉንም ተቋማት ተሳትፎ የሚሻ መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው ገልጸዋል፡፡
ኤጀንሲው ከዳያስፖራው ማህበረሰብ ትብብር የሚፈልጋቸው በርካታ ጉዳዮች መኖራቸውን ገልጸው÷ የእውቀት ሽግግር በዋናነት ይጠቀሳል ብለዋል፡፡
የዳያስፖራው ማህበረሰብ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውንም ከዳያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

