Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአማራን ህልውና ለማስጠበቅ የወገን ጦር ሁሌም በተጠንቀቅ ላይ ነው – ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራን ህልውና ለማስጠበቅ የወገን ጦር ሁሌም በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ አስታወቁ፡፡
በህልውና ዘመቻው ተሳትፈው የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ለዘመቱ አካላት በጎንደር ከተማ የፋሲል አብያተ መንግስት ግቢ ውስጥ የንጉሥ እራት መርሀ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡
ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ባደረጉት ንግግር÷ አንፃራዊ ሰላም እና እፎይታ ለሰጡን ለመከላከያ፥ ልዩ ኃይል፥ ፋኖና ሚሊሻ ዛሬ የምስጋና ቀን ነው ብለዋል።
“የኢትዮጵያን አንድነት ለማስቀጠል እንዘጋጅ፤ ጠላቶቻችን ብዙ ናቸው” ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ፥ ውስጣዊ አንድነታችንን በማጠናከር የአንድነትና የሰላም ችግሮችን ልንፈታ ይገባል ብለዋል።
የህልውና ዘመቻው የመጀመሪያ ዙር እንዲጠናቀቅ ህዝቡ ያደረገው ተጋድሎ ሊደነቅ ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ አሁንም ክልሉ ተጨባጭ የጥቃት ሙከራዎች ሊደረጉበት ስለሚችል የአማራን ህልውና ለማስጠበቅ የወገን ጦር ሁሌም በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ ነው የገለጹት።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የክልሉ ከተሞች የውስጥ ሰላማቸውን እና አንድነታቸውን በመጠበቅ የቀደመ ልማታዊ ጉዟቸውን ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
በመርሀ ግብሩ ከፍተኛ የፌደራል፣ የክልል እና የዞን የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ ጀግኖች የሠራዊት አባላት ተገኝተዋል።
ምናለ አየነው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version