Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ግብርና እና የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴሮች ድጋፍ ለሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች ያስገነቧቸውን መኖሪያ ቤቶች አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና እና የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴሮች በአማራ ክልል እና በአዲስ አበባ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ቤተሰቦች ያስገነቧቸውን መኖሪያ ቤቶች አስረከቡ፡፡
ግብርና ሚኒስቴር በአማራ ክልል መራዊ ከተማ ድጋፍ ለሚሹ አምስት አባወራዎች ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች አስረክቧል፡፡
የርክክብ መርሃ-ግብሩም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አመራሮች እና የመራዊ ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
የተገነቡት ቤቶች ለአንድ ቤተሰብ የሚያስፈልጉትን መሠረታዊ ፍላጎቶችን ያሟሉ እና ዘመናዊ ሆነዉ የተገነቡ ሲሆን፥ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገባቸው ተገልጿል።
በተመሳሳይ÷ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ 12 ቤተሰቦች አስረክቧል፡፡
ሚኒስቴሩ ግንባታውን ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ጋር በመተባበር ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር አባላት በተገኘ የገንዘብ፣ የሙያ እና የአይነት ድጋፍ ማስገንባቱም ነው የተነገረው፡፡
ለቤቶቹ ግንባታ 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጓል ነው የተባለው፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like
Comment
Share
Exit mobile version