Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ላይ የተጠነሰሰው ሴራ ከውስጥም ከውጭም ሀገሪቱን የማፍረስ ግብ ነበረው – የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው የህወሃት ቡድን በተካሄደው ወረራ ከውስጥም ከውጭም ኢትዮጵያን የማፍረስረስ ግብ ያለውና ሚዲያዎችን በመጠቀም ጭምር ከባድ ሴራ የተጠነሰሰበት እንደነበር ምሁራን ተናገሩ፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያ ዘላለም ግዛቸው÷ኢትዮጵያ በውስጥም በውጭ የተደቀነባት ጫና በኢኮኖሚውና በፖለቲካው ዘርፍ ሚዲያዎችን በመጠቀም ጭምር ሀገሪቱን ለማፈራረስ ከባድ ሴራ የተወጠነበት እንደነበር ነው ያብራሩት፡፡
እነዚህ የውስጥና የውጭ ሃይላት በሌሎች ሀገራት ላይ ያደረጉትን የማፍረስ የሴራ ፖለቲካ ሸርበው ቢነሱም፥ ኢትዮጵያ ግን እንደሌሎቹ ሀገራት በቀላሉ የምትንበረከክ አገር እንዳልሆነች ዳግም አስመስክራለች ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጠላቶች ያሰቡት እንዳይሆን ያደረገው የህዝቦቿ አንድነት መሆኑን የገለጹት ባለሙያው፥ ነገር ግን ሴራው በዚሁ ይቆማል ተብሎ የማይጠበቅ በመሆኑ አሁንም የህዝቡ አንድነትና ትግሉ ሊቀጥል እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ህወሓት በከፈተብን ጦርነት ካደረሰብን ስብራት በላይ ታላላቅ ሀገራትና መንግስታት ምን ዓይነት ጫና ሲያሳድሩብን እንደነበረም አውስተዋል፡፡

እኛን ለማድቀቅ በማሰብ ኢኮኖሚያችን ላይ ያደረጉት ተፅዕኖ ቀላል አይደለም ያሉት አቶ ዘላለም፥ በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ላይ ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩብን፥ የራሳችንን አቅም ማሳደግና መበልፀግ ሲገባን ያለንን የተፈጥሮ ሀብት ተጠቅመን ባለመስራታችን ነው ብለዋል፡፡

በዚህም በተለይም ከልመና ወጥቶ በራስ አቅም መቆም እንዲቻል ማድረግ ዘላቂ መፍትሔ ሆኖ ይቀመጣል ብለዋል፡፡

በታሪኩ ለገሰ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version