Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጋምቤላ ክልል የበጋ ወቅት የተፋሰስ ልማት ስራ በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የበጋ ወቅት የተፋሰስ ልማት ዘመቻ በማጃንግ ብሔረሰብ ዞን መንገሺ ወረዳ ዛሬ በይፋ ተጀመረ።

በዘመቻው ከ49 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ሥራዎች እንደሚከናወኑ ተመላክቷል።

ዘመቻው ለአንድ ወር እንደሚቆይ የተገለጸ ሲሆን÷ ከ250 ሺህ የሚበልጡ ነዋሪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በማስጀመሪያ ሥነ- ሥርዓቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version