አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በሽብር ቡድኑ ህወሃት ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚሆን ገቢ ከባለሀብቶች ማሰባሰብ መጀመሩንና በዛሬው ዕለትም ከ12.7 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ገለጸ።
የክፍለ ከተማው አስተዳደር ይህንኑ ሀብት ማሰባሰቡን ታሳቢ ያደረገ መርሐ ግብር በክፍለ ከተማው ከሚገኙ የሪል እስቴት፣ የሞልና የህንፃ ባለቤቶች ጋር በኢትዮጵያ ሆቴል ማዘጋጀቱን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘመኑ ደሳለኝ ተናግረዋል።
በዕለቱም የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድን ፎቶ በ1 ሚሊዮን ብር ጨረታ ጊፍት ሪል እስቴት ሲያሸንፍ፣ ደስታ ኢንጂነሪንግ PLC የግንባታ ዲዛይኑን ጨምሮ 10 .5 ሚሊዮን ብር በሚያወጣ ወጪ የፈረሰ ት/ቤት ለመገንባት ቃል ገብቷል።
በአጠቃላይ በዕለቱ ከ12.7 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል።
በቀጣይም ባለሀብቶችን በማስተባበር ሀብት የማሰባሰቡ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ዘመኑ ደሳለኝ መናገራቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

