Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሀገርን ከመፍረስ ታድጓል- ሌ/ጀነራል መሃመድ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰራዊታችን በመስዋዕትነቱ ህዝባችንን ከመከራ እንዲሁም አገራችንን ከመፍረስ ታድጓል ሲሉ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል መሃመድ ተሰማ ተናገሩ፡፡
 
ሌተናል ጀነራል መሃመድ ተሰማ ከምስራቅ ዕዝ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱም ጁንታውንና ሸኔን ለመደምሰስ በተደረገው አገራዊ ርብርብ የሰራዊታችን አካል የሆነው የምስራቅ ዕዝ የሰራዊት አመራርና አባላት የከፈሉት መስዋዕትነት በህዝባችን ላይ ተደቅኖ የነበረውን የህልውና ስጋት በመቅረፍ ነፃነቱን ያጎናፀፈ ነው ሲሉ ሌተናል ጀነራል መሃመድ ተናግረዋል፡፡
 
በዚህም አገራችንን ከመፍረስ ማዳን መቻሉን ነው የገለጹት፡፡
 
በርካታ ከተሞችን በመቆጣጠር ህዝባችንን ሲዘርፍና ሲገድል የነበረውን ሽብርተኛ በመደምሰስ፣ በመማረክና በማቁሰል ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንዲደርስበት በማድረግ የተረፈው ሃይሉም ወደ መደበቂያው እንዲሸሽ ተደርጓል ብለዋል፡፡
 
ህዝባችን ከጎናችን ተሰልፎ ያደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ የድሉ ዋነኛ ምንጭ በመሆኑ በቀጣይም ሽብርተኛውን ህወሃት እስከ መጨረሻው ለመደምሰስ የሚያስችሉ ወታደራዊ ዝግጁነታችንን የማጠናከር ፣ በውጊያው የታዩ ጠንካራ ጎኖቻችንን የማጎልበት እና የታዩ ጥቃቅን ስህተቶችን በማረም ላይ ያተኮሩ ውይይቶችን በማድረግ አንድ አይነት አረዳድ በመፍጠር በቀጣይ መንግስትና ህዝብ ለሚሰጠን ግዳጅ መዘጋጀት አለብን ሲሉ መናገራቸዉን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
Exit mobile version