አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ የማዕድን ኤግዚቢሽን እና ፎረም በአዳማ ተከፈተ።
ኤግዚቢሽኑን እና ፎረሙን የክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በጋራ ከፍተውታል።
የኢፌዴሪ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክትም፥ የኦሮሚያ ክልል የማዕድን ሀብት የተከማቸበት የማዕድን ጎተራ መሆኑን ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ “ጎተራውን በሁሉም መልኩ ተጠቅመን የህዝባችንን ህይወት ሊለውጥ፤ ሀገራችን ከሀብቱ ልትጠቀም ይገባል” ብለዋል።
ኤግዚቢሽኑ በማዕድን ዘርፍ ያለንን ተስፋ ሰፊና ብሩህ መሆኑን የሚያሳይ መሆኑን እና በጥረት ተስፋውን በተግባር እንዲገለፅ እንደሚደረግም ነው ያረጋገጡት።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!