Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ምስራቅ ዕዝ በውጊያ የተሻለ ውጤት ላመጡ እና የመቆያ ጊዚያቸውን ለሸፈኑ አባላቱ የማዕረግ ዕድገት ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምስራቅ ዕዝ በውጊያ የተሻለ ውጤት ላመጡ እና የመቆያ ጊዚያቸውን ለሸፈኑ የሰራዊት አመራሮችና አባላት የማዕረግ ዕድገት ሰጠ፡፡
አሸባሪው የህወሃት ቡድን በከፈተው ጦርነት ላይ በመዋጋትና በማዋጋት ፣ ጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንዲደርስበት ያደረጉና የመቆያ ጊዚያቸውን ለሸፈኑ አመራሮችና አባላት ነው የማዕረግ ዕድገት የተሰጠው፡፡
ማዕረግ ሲጨምር የበለጠ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የሚጨምር መሆኑን የገለጹት የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌ/ጀነራል መሐመድ ተሰማ ÷ ̋ የቀጣይ ተልዕኳችሁን በላቀ ሁኔታ ለመወጣት እራሳችሁን የምታዘጋጁበት እና የምትወጡበት ፣ የአመራር ብቃታችሁን ፣ ልምዳችሁንና ክህሎታችሁን የምታሳድጉበት̋ ነው” ብለዋል፡፡
በተቋሙ ከፍተኛ እምነት ተጥሎባችሁ የተሰጣችሁ እድገት መሆኑን በመገንዘብ ለአገራችሁና ለህዝባችሁ ታማኝ በመሆን ግዳጃችሁን በፅናትና በጀግንነት መወጣት ይገባችኋልም ነው ያሉት፡፡
መንግስትና ህዝብ የሰጠንን ተልዕኮ በድል አድራጊነት ፈፅመን ለቀጣይ ግዳጅ እየተዘጋጀን ባለንበት ወቅት የተሰጣችሁ የማዕረግ ዕድገት ሽልማት ተጨማሪ አቅም ይሆናችኋል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በየወቅቱ ሊያጋጥም የሚችለውን የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ መሰናክል ለማለፍ የሚያስችል ብቃት፣ የአመራር ሳይንስና ጥበብ እንዲሁም ፈጠራ በመጠቀም በውጤታማነት መወጣት ከእናንተ ይጠበቃል ሲሉም አሳስበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version