Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካሪ ኮሚቴ ሁለት አጀንዳዎችን አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ጥር 17፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካሪ ኮሚቴ ሁለት አጀንዳዎችን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል ፡፡
አጀንዳዎቹ የማሕበረሰብ ጤና አቀፍ መድህን ረቂቅ አዋጅ እና የ2014 በጀት ዓመት ተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጆች መሆናቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ገልጸዋል ፡፡
ምክትል አፈ-ጉባኤዋ በማሕበረሰብ ጤና አቀፍ መድህን ረቂቅ አዋጅ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ረቂቅ አዋጁ ህክምና ማግኘት ለማይችሉ የሕብረሰተብ ክፍሎች ፍትሃዊ ፣ ተደራሽ እና ጥራት ያለው የጤና ሽፋን በመስጠት እንዲታከሙ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በ2014 በጀት አመት ተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅ አስፈላጊነት ላይም ወ/ሮ ሎሚ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ፥ ረቂቅ ረቂቅ አዋጁ የተቋረጡ እና በጅምር ላይ ያሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ለማስቀጠል እንዲሁም በኮሮና ቫይርስ እና በጦርነቱ ምክንያት የወጡ ወጪዎችን ለመሸፈን እንደሚውል ጠቅሰዋል።
ለዚህም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ታይቶ 122 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት እንደቀረበም ነው የገለጹት፡፡
የአማካሪ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው አጀንዳዎቹ ፥ ተገቢ እና የሕዝቡን ችግር ለመፍታት ሚናቸው የጎላ እንደሆነ አብራርተዋል ፡፡
አጀንዳዎቹ በቀጣዩ የምክር ቤት ጉባኤ ቀርበው ምክር ቤቱ እንደሚወያይባቸው ምክትል አፈ-ጉባኤዋ መግለጻቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version