አዲስ አበባ፣ጥር 17፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድን ጥሪ ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት የመጡ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጅማ ከተማን ጎበኙ።
አባላቱ ወደ ጅማ ከተማ ሲገቡ የከተማዋ ከንቲባ፣ የጅማ ዞን ምክትል አስተዳደሪ፣ የእምነት አባቶችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል አባላት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ነጂብ ራያ፥ ሀገራችን ፈተና ውስጥ በገባችበት ወቅት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሀገራቸው አምባሳደር በመሆን በዲፕሎማሲው ዘርፍ ያበረከቱት አስተዋጽኦ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የዳያስፖራው ማህበረሰብ ገንዘብ በማሰባሰብ ለጅማ ከተማ ልማት ባደረጉት ድጋፍ በ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የመማርያ ክፍሎች መገንባታቸውን እና ህፃናት የሚማሩበት ‘ቡኡረ ቦሩ’ ትምህርት ቤትን በጅማ ከተማ እያስገነቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የዳያስፖራ አባላቱ ላደረጉት ድጋፍምም ከንቲባው ምስጋና አቅርበዋል።
የጅማ ዞን ምክትል አስተዳሪ አቶ የሱፍ ሻሮ በበኩላቸው፥ በኢንዱስትሪ፣ በግብርና እና በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፎች መሳተፍ ለሚፈልጉ የዳያስፖራ አባላት በከተማውም ሆነ በዞኑ ምቹ ሁኔታ መኖሩን አስረድተዋል።
በዚሁ ጊዜም ከ6 ዓመታት በፊት በማህበር ተደራጅተው 7 ሚሊየን ዶላር ለቆጠቡ 120 የዳያስፖራ አባላት ሪል ስቴት የሚገነቡበት የመሰረት ድንጋይ ተጥሏል።
ዳያስፖራዎቹ በጉብኝታቸው በእድሳት ላይ የሚገኘውን የንጉስ አባ ጅፋር ቤተመንግሥትን እና ጅማ ዩኒቨርሲቲን ጎብኝተዋል።
በሙክታር ጠሃ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!