Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጅግጅጋ ባለፉት ሶስት ዓመታት ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት የሆኑ መንገዶችን ተዘዋውረው ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጅግጅጋ ከተማ ከለውጡ ወዲህ ባለፉት ሶስት ዓመታት ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁ የአስፋልት መንገዶችን ተዘዋውረው ጎበኙ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድን ጨምሮ ከሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ለአገልግሎት የበቁት የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፣ የ05 ቀበሌ፣ የዱአሌ እንዲሁም የሼክ ኑር ኢሴና የአየር ደጋ የአስፋልት መንገዶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
እንደ ሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በክልሉ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version