አዲስ አበባ፣ጥር 17፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በ600 ሚሊየን ብር የተገነባው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ዛሬ ተመረቀ።
የዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር የሻረግ ጌታነህ፥ ካምፓሱ በዚህ ዓመት 2 ሺህ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጁ ነው ብለዋል።
ዛሬ የተመረቀው አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ባለ 4 ወለል 3 ህንፃዎች ያሉት ሲሆን ፥ 44 የመማሪያ ክፍሎች እንዳሉትም ገልጸዋል።
የሃኪም ግዛው መታሰቢያ ሆስፒታልን ጨምሮ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጥቶበታልም ነው ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቷ።
18 ላቦራቶሪዎችን የያዘው ሀኪም ግዛው ሆስፒታል ከዚህ በፊት የነበረውን የክፍል ጥበትና የምርምር ላቦራቶሪዎች እጥረትን የሚፈታ ነው ተብሎለታል።
በሳምራዊት የስጋት
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!