Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኦሮሚያ ከ700 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት ከ700 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ሥራ መፍጠሩን የኦሮሚያ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው በ2014 የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የክልሉን የሥራ ዕድል አማራጮች ከመለየት ጀምሮ የመሥሪያና መሸጫ ቦታዎች፣የብድር አቅርቦት በማመቻቸትና በአቅም ግንባታ ላይ በማተኮር መሥራቱ ተመላክቷል፡፡
የቢሮው ኃላፊ አህመድ ኢድሪስ በወቅቱ እንደገለጹት ÷በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት ከ700 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል ተፈጥሯል።
ዜጎችን ወደ ስራ ለማስገባት ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ብድር መመቻቸቱን ጠቁመው ከ29 ሺህ ሄክታር በላይ መሬትም በማኅበር ለተደራጁ ወጣቶች መተላለፉን አስታውቀዋል።
ሥራ ከተፈጠረባቸው ዘርፎች መካከል በግብርና መስክ 400ሺህ ዜጎች መሰማራታቸውን የገለጹት የቢሮ ሃላፊው ÷ የሰብል ልማት፣ እንስሳት ዕርባታና ማድለብ፣ ዶሮ እርባታ፣ ንብ ማነብና የተፈጥሮ ሐብት ልማት ዋናዎቹ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ግንባታ ፣ማዕድን ልማት፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ አገልግሎትና አነስተኛ ንግድ ሌሎች ሥራ የተፈጠረባቸው ዘርፎች ናቸው ተብሏል፡፡
የብድር አቅርቦትና ፍላጎት ያለመጣጣም፣ በቂ የመስሪያና መሸጫ ቦታ አለማቅረብ፣ የሊዝ ማሽን ኪራይና ብድርን በወቅቱ አለመመለስ በሥራ ፈጠራ ሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንደነበሩ መመልከቱን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version