Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሐረሪ ክልል አርሶ አደሩ ከዝናብ ጠባቂነት ተላቆ ለበጋ መስኖ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ለበጋ መስኖ ልማት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሚስራ አብደላ ገለጹ።
በሐረሪ ክልል በ36 ሚሊየን ብር እየተከናወነ የሚገኘው የ6 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የመስኖ ፕሮጀክት እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዘንድሮው ዓመት አርሶ አደሩ ከዝናብ ጠባቂነት ተላቆ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተለይም ለበጋ መስኖ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ በሚገኙ በሶፊና ኤረር ወረዳዎች በ36 ሚሊየን ብር 6 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የመስኖ ፕሮጀክት እየተጠናቀቀ መሆኑን ነው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ የተናገሩት።
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም 531 ሄክታር መሬት እንደሚያለማ የገለጹት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ ÷ 1 ሺህ አርሶ አደሮችንም ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ነው የተናገሩት።
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በክልሉ ከውሃ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮችን ይቀርፋል ያሉት ደግሞ የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሻሜ አብዲ ናቸው።
ቀደም ሲል በቂ ውሃ ስለማያገኙ የሚያመርቱት ምርት ውስንና አነስተኛ ከመሆኑም ባሻገር፥ ውሃን ለማግኘት በርካታ ልፋትና ውጣ ውረድ ሲገጥማቸው መቆየቱን አርሶ አደሮቹ ተናግረዋል።
የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት አትክልት፣ ፍራፍሬና ሌሎች የገቢ ማስገኛ ምርቶችን ለማምረት እንደሚያስችል ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version