Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከተማ አስተዳደሩ በጉጂ ዞን በድርቅ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በድርቅ ምክንያት ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ፡፡

የአስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉጂ ዞን በድርቁ ጉዳት ለደረባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እና በድርቁ ምክንያት እየተጎዱና እየሞቱ ላሉት እንስሳት የሚሆን የሳርና የመኖ እንዲሁም የውሃ ማጠራቀሚያ ሮቶ ድጋፎችን ለዞኑ አስተዳደር አስረክበዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች በድጋፍ ርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት፥ የዛሬው ድጋፍ ዋና አላማ አብረናቸው መሆናችንን ለማሳየትና ፍቅራችንን ለመግለፅ ነው ብለዋል።

ጉጂ አንድም በድርቅ ሁለትም ደግሞ በፀጥታ ችግር እየተሰቃየ ነው ያሉት ከንቲባዋ፥ አካባቢው ወደ ተረጋጋ ሁኔታ እስኪመለስ ድረስ አንለያቸውም፤ ድጋፉም ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።

በዞኑ ባጋጠመ ችግር ምክንያት ህብረተሰቡ፣ እንስሳቶች፣ ግመሎችና ፍየሎች እየተጎዱ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የጉጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ኦዶ ናቸው፡፡

ዋና አስተዳዳሪው ለቀረበው አገራዊ ጥሪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሰጠው ምለሽ ምስጋና ማቅረባቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version