አዲስ አበባ፣ ጥር 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ወረርሽኝ እንዳይቀሰቀስ እየሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ።
ድርቁ ባስከተለው የምግብ እና የውሃ እጥረት እንዲሁም በዓየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ወረርሽኝ የመከሰት እድሉ ሰፊ ነው ተብሏል ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ፥ በድርቁ ሳቢያ እንደ ኮሌራ እና ኩፍኝ ያሉ ወረርሽኞች እንዳይቀሰቀሱ ክትባት መሠጠት መጀመሩን አስታውቀዋል ።
በሶማሌ ክልል በሚገኙ አራት ወረዳዎችም ለ200 ሺህ ሰዎች የኮሌራ ክትባት መሰጠቱን ሚኒስትሯ ገልጸዋል ።
የኩፍኝ ወረርሽኝም የተከሰተባቸው የተወሰኑ አካባቢዎች ስለነበሩ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ቶሎ ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል።
በቅርቡ የኩፍኝ ክትባት ከአምስት አመት በታች ላሉ ህጻናት መስጠት እንደሚጀመርም አስታውቀዋል ።
እስካሁን ባለው መረጃ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ከዚህ ቀደም ከነበረው ባይጨምርም ቀስ በቀስ ሊከሰት ስለሚችል አስፈላጊ የአልሚ ምግብ ድጋፍ እና ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን የመለየት ሥራ እየተሰራ ነውም ብለዋል።
በአልዓዛር ታደለ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

