Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ተቋማዊ ነፃነት እንዲሳካ ለማገዝ የተደራጀው ግብረ ሃይል ወደ ሥራ ገባ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነፃ እና እራሱን የቻለ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ የተደራጀው ግብረ ሀይል ወደ ስራ መግባቱ ተገለፀ።

የትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሥራ አመራር ቦርድ  ጋር የግብረ ሃይሉን የሥራ ማስጀመሪያና ትውውቅ መድረክ አካሂደዋል፡፡

መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነጻነት ተጎናፅፈው መስራት እንዲችሉ   ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቋማዊ ነፃነት ኖሮት መልሶ እንዲደራጅ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

በውይይቱም የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፊሰር ብርሃኑ ነጋ፥ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ተቋማዊ ነጻነት መስጠት ከመንግስትም ከማህበረሰቡም ስምምነት የተደረሰበት መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

ይህ የለዉጥ ስራ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተቃማዊ ነጻነትን ማምጣት ብቻ ሳይሆን፥ ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተቋማዊ ነጻነት የሚሰጥ  መሆኑንም ገልፀዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነፃነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሮ ወደ ሌሎች ከፍተኛ ተቋማትም የሚስፋፋ መሆኑም ተገልጿል።

በWይይቱ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ፣ የማኔጅመንት አባላት እና የተመረጡ ግብረ ሀይሉ አባላቶች መሳተፋቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version