ያሉት
አዲስ አበባ ፣ጥር 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል አሸባሪው የህወሓት ቡድን 3 ሺህ 228 የኅብረት ሥራ ማኅበራትንና ዩኒየኖችን መዝረፉንና ማውደሙን የክልሉ የኀብረት ሥራ ማኀበራት ማስፋፊያ ኮሚሽን አስታወቀ።
በድኑ በህዝብ ሐብትና ንብረት ላይ ያደረሰው ዘረፋና ውድመት ከ25 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚገመት ኮሚሽኑ ገልጿል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ልጃለም ገዳሙ ÷ ቡድኑ 3 ሺህ 127 የኅብረት ሥራ ማሥበራትን፣ 22 ዩኒየኖችንና 79 የዞንና የወረዳ ሥብረት ሥራ ማኅበራት አደራጅ ጽህፈት ቤቶችን መዝረፉንና ውድመት ማድረሱንም ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ስምንት የእርሻ ትራክተሮችን ጨምሮ በርካታ የመስክ ተሽከርካሪዎችን፣ የዓሳ ማስገሪያ ጀልባዎችንና ሌሎች የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን ዘርፏል፣ ያልቻለውን ደግሞ አውድሟል ነው ያሉት ኃላፊው።
በኅብረት ሥራ ማኅበራቱ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ ከ9 ሺህ በላይ ወገኖች ከሥራ ገበታ ውጭ እንዲሆኑ ማድረጉንም አስረድተዋል።
ማኅበራቱን ወደ ሥራ ለማስገባት ክልሎች፣ አቅም ያላቸው አቻ ዩኒየኖችና የህብረት ስራ ማህበራት እንዲሁም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ማኅበራቱን፣ ዩኒየኖችንና ጽህፈት ቤቶችን ወደቀደመ ስራቸው ለመመለስ 30 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ እንደሚያስፈልግም ማብራራቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን