አዲስ አበባ ፣ጥር 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት ያግዛሉ የተባሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ማህበራት እውቅና አግኝተው ወደ ስራ ገቡ።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እገዛ የተቋቋሙት ማህበራቱ÷ የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ማህበር፣ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት ሰጪዎች ማህበር እና የኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር መሆናቸው ተገልጿል።
በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች ጠንካራ ማህበር ኖሯቸው የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ መደገፍ እንዳለባቸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት ሊሳካ የሚችለው የግሉ ዘርፍ በመሪነት ሲሳተፍ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ÷ ለስኬቱም የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚውን ለመምራት የሚያስችል አቅም ሊፈጥርና ሊቀናጅ ይገባል ነው ያሉት፡፡
ማህበራቱ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን÷ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን