Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሀገር አቀፍ ደረጃ 40 ሚሊየን ዜጎችን የጤና መድን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል-የጤና መድን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ 40 ሚሊየን ዜጎችን የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ገለጸ፡፡
በኢትዮጵያ ከ52 ሚሊየን የሚልቁ ዜጎችን የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አባል በማድረግ የጤና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ጤና መድን አገልግሎት፥ እስከ አሁን 40 ሚሊየን ዜጎችን ተጠቃሚ  አድርገናል ብሏል፡፡
በኢትዮጵያ ጤና መድን አገልግሎት የአባላት ምዝገባና መዋጮ ዳይሬክተር አቶ ጉደታ አበበ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በዘርፉ የሚታዩ ውስንነቶችን በመቅረፍ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡
በዘርፉ ጎልተው የሚታዩ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እየተሰራ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፥ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡን ገልጸዋል፡፡
በታለ ማሞ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version