አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 35ኛውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ የምናስተናግደው ለኮቪድጥ- 19 የወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ እንደሚሆን ተገለጸ፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሠ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ዮናስ ዘውዴ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝተው በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
በኮቪድጥ 19 መከሰት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በቀጣይ ስምንት በአዲስ አበባ ሲካሄድ÷ ለጉባዔው የሚመጡ እንግዶቻችንን ስናስተናግድ ለኮቪድ- 19 መከላከል የወጡትን መመሪያዎች ተግባራዊ በማድረግ ነው ብለዋል።
ስብሰባዎች ሲካሄዱ ቁጥርን መሰረት ባደረገ መልኩ መሆን እንደሚገባቸው እና ተቋማት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ከአፍሪካ ኅብረት እና ከአፍሪካ የበሽታወች መቆጣጠር እና መከላከል ድርጅት (CDC) ጋር በመሆን እየሠራን ነው ብለዋል።
የቢሮ ሃላፊው ዮናስ ዘውዴ በበኩላቸው፥ ከዚህ በፊት በሆቴሎች፣ በአገልግሎት መስጫ ተቋማት እና በትራንስፖርት አገልግሎቶች ላይ ተግባራዊ ሲደረጉ የነበሩት የኮቢድ-19 መከላከያ መመሪያዎች በአዲስ አበባ ከተማ በጥብቅ ተግባራዊ ይደረጋሉ ነው ያሉት።
ኅብረተሰቡ ለእንግዶቹ መልካም የሆነ አቀባበል እንዲያደርግ እና 500 የሚሆኑ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመተባበር እንዲሰሩም ጥሪ ቀርቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን