አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በ150 ሚሊየን ብር የተገዙ ተሽከርካሪዎችን ለክልሎች በድጋፍ መልክ መስጠቱን ገለጸ።
ድጋፉን የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ከሚሽን ምክትል ኮሚሸነር ነሲቡ ያሲን ለክልል ተወካዮች የመኪኖችን ቁልፍ አስረክበዋል።
ተሽከርካሪዎቹ የተገዙት በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን፥ በዚህም 24 መኪናዎችን ለአምስት ክልሎች አስረክበዋል።
በዚህም መሰረት አምስት ለአማራ፣ ሰባት ለኦሮሚያ፣ አራት ለሶማሌ፣ አራት ለደቡብ፣ ሁለት ለሲዳማ ክልሎች እና ሁለት ደግሞ ለብሔራዊ የአደጋ ስጋት አመራር ስራ ኮሚሽን ተከፋፍሏል።
እንዲሁም 60 ሞተር ሳይክሎች 30 ለሶማሌ ፣ 24 ለደቡብና 6 ለሲዳማ ክልሎች ማስጠቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

