አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎትን ከድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ጋር ጎብኝተዋል፡፡
ለረጅም ዓመታት የሰው ሰራሽ አካልና ድጋፍ በመስራት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት በቅርቡ በአዲስ መልክ እየተደራጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ዶክተር ሊያ አሁን ካለበት በተሻለ በአዳዲስ ማሽነሪና ቴክኖሎጂ ለማደራጀት ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች እና ከቱርክ ከመጡ ቴክኒካል ባለሙያዎች ጋር በመሆን ተቋሙን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ከመግባታቸው በፊት አጠቃላይ በተቋሙ ውስጥ ያሉትን የመትከያ ቦታዎችና የተቋሙን አጠቃላይ ዝግጅት ተመልክተዋል።
በቀጣይነት ማሽኖቹን እንዴት ማስገባት እንደሚቻል እና ስልጠናዎችን ለመስጠት በሚያስችለው ሂደት ላይ መምከራቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

