Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኩዌት ወደ ኢራቅ የምታደርገውን በረራ ማቋረጧን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከትናንት በስተያ የባግዳዱን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዒላማ ያደረገ የሮኬት ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ ኩዌት ወደ መዳረሻው የሚደረግ በረራ ማቋረጧን አስታውቃለች፡፡

የኩዌት አየር መንገድ ውሳኔው የተላለፈው በኢራቅ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ለመንገደኞች ደኅንነት አስጊ በመሆኑ ነው ብሏል፡፡

አርብ ዕለት በባግዳድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተፈጸመው ሥድስት የሮኬት ጥቃቶች በሁለት የመንገደኖች አውሮፕላኖች ላይ ጉዳት ደርሷል ነው የተባለው፡፡

የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ አል-ካዲሚ ÷ አየር መንገዳችን ላይ የተፈጸመው ጥቃት የሀገሪቷን መልካም ሥም ለማጠልሸት ነው፤ ለአደገኛ ድፍረታቸውም አጸፋዊ ምላሽ እንደሚያገኙ ቃል እገባለሁ ነው ያሉት፡፡

ለተፈጸመው ጥቃት እስካሁን ሃላፊነቱን እወስዳለሁ የሚል አካል አልተሰማም ተብሏል፡፡

የባግዳድ አየር ማረፊያ ካምፕ ቪክትሪ ተብሎ ከሚጠራው የአሜሪካ ዓየር ኃይል ማዘዣ በቅርብ ርቀት ላይ ነው የሚገኘው፡፡

የአሜሪካው ዓየር ኃይል ማዘዣ በቅርብ ወራት በርካታ የሮኬት ጥቃቶች ተፈጽመውበታል፡፡

አሜሪካም ÷ በማዘዣው ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ሚቃጡት በኢራን ከሚደገፉ ታጣቂዎች ነው ስትል እየከሰሰች እንደምትገኝ የዘገበው አናዱሉ ነው፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version