Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ብሔራዊ መግባባት የብልጽግናችን ሞተር ነዉ – ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለምታደርገው የብልጽግና ጉዞ መሰረቱ ብሔራዊ መግባባት መሆኑን የሲዳማ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።

የክልል፣ የከተማ እና በተለያዩ እርከኖች ላይ ያሉ አመራሮች በሀገራዊ የሠላምና ፀጥታ ጉዳይ ላይ በሐዋሳ ከተማ መክረዋል፡፡

በምክክር መድረኩ የሲዳማ ክልል ርዕሰ – መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ÷ ተግባቦት ያልፈጠርንባቸዉ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ያሉ በመሆኑ ትኩረት በመስጠት ልንሰራባቸዉ ይገባል ብለዋል።

ርዕሰ-መስተዳድሩ ÷ አባቶች ችግሮችን በምክክርና በይቅርታ እንደተሻገሩት ሁሉ እኛም ከእነሱ ተሞክሮ ወስደን ችግሮችን በውይይት የማናልፍበት ምክንያት የለም ብለዋል።

የግጭት ምንጭ የሚሆኑ ጉዳዮችን አስቀድመን በመለየት ፤ ኅብረተሰቡን የሚያቀራርቡ እና አንድነታቸዉን የሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

በመድረኩ የተገኙት በሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን ÷ በመድረኩ ሀገራዊ መግባባትና ሰላም ማስፈን የሚያስችሉ ጉዳዮች መክረን የጋራ አቋም የምናስቀመጥበት ይሆናል ሲሉም ተናግረዋል።

በተለያዩ ቦታዎች ምክክር ሲደረግበት የነበረዉ የሰላም ፖሊሲ ላይ አሁንም የበለጠ መሻሻል የሚገባቸዉን ሃሳቦች ላይ ግብአት የምንሰበስብበት ነውም ብለዋል፡፡

በመድረኩ ክልሎችና የከተማ አስተዳደር አካላት በቅንጅት በመንቀሳቀስ የዜጎችን ሰላም መንከባከብ፣ ማጎልበትና ማስጠበቅ የሚችሉበትን አሰራሮች ያስቀምጣሉ ተብሏል።

መሰል መድረክ በየሩብ ዓመቱ መደበኛ በማድረግ በአፈጻጸም ዉስጥ የሚያገጥሙ ችግሮችን ለማቃናት መግባባት ላይ የሚደረስ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን ተናግረዋል።

በጀማል ከዲሮ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version