Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

100 በጎ ፈቃደኛ የጤና ባለሙያዎች ለሕክምና ድጋፍ ወደ አማራ ክልል ተሰማሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ የሕክምና ድጋፎች ለመስጠት አንድ መቶ በጎ ፍቃደኛ የጤና ባለሙያዎች ወደ አማራ ክልል ተሰማሩ።

የሕክምና ባለሙያዎቹ ከጥር 22 እስከ 29 ቀን 2014 በአማራ ክልል የሕክምና ምርመራ፣ ሕክምናና የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ፤ መድኃኒትም ያቀርባሉ ተብሏል።

ሸዋሮቢት፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ ሐይቅ፣ ባቲ፣ ኩታበር፣ ቆቦና ወልድያ በጎ ፍቃደኞቹ የሕክምና ድጋፋቸውን የሚያቀርቡባቸው የአማራ ክልል ከተሞች ናቸው።

የበጎ ፍቃደኞቹ ቡድን በጅማ ዩኒቨርሲቲ የምረቃ ተማሪዎች ኅብረት አስተባባሪነት ከተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች የተውጣጡ የሕክምና ባለሙያዎችን ያቀፈ ነው።

የበጎ ፍቃድ አገልግሎቱ በኮምፓሽን ኢንተርናሽናልም አስተባባሪነት የሚሰጥ ሲሆን÷ ሰን ራይዝ ዴቨሎፕመንት ኢትዮጵያም አጋር ድርጅት ነው።

በጎ ፍቃደኞቹ ሌሎች በጤና እና በሌሎችም የሙያ መስኮች ያሉ ወጣቶች ወደ ሥፍራው በማቅናት ሠብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version