Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአማራ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ።
የክልሉ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኀላፊ ግዛቸው ሙሉነህ እንዳስታወቁት፥ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስድስተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የስራ ዘመን ስምንተኛ አስቸኳይ ስብሰባ ወቅታዊና አሁናዊ ክላላዊ ሁኔታችንን በመገምገም የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን በዝርዝር በመገምገም የቀጣይ የትኩረት መስኮችን አስቀምጧል።
በተጨማሪም ሶስት የተለያዩ ደንቦችን መርምሮ ማፅደቅ ማለትም፣ የአሠሪና ሠራተኛ ባልስልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ መርምሮ ማፅደቅ፥ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን ማቋቋሚያ አዋጁ መርምሮ አጽድቋል።
በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ማቋቋምና ልማት ፈንድ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የማቋቋሚያ ደንብ መርምሮ ማጽደቅ በሚሉ አጀንዳዎች ምክር ቤቱ በጥልቀት የተወያየ ሲሆን፥ ሁሉም አጀንዳዎች ላይ በስፋት ተወያይቶ ማሻሻያዎችን በማድረግ በሙሉ ድምጽ አጽቋል።
የተወሰኑ ውሳኔዎችም ከዛሬ ጥር 22/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆኑ ምክር ቤቱ የወሰነ ሲሆን በተለይም በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ማቋቋምና ልማት ፈንድ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚቆይና ሀብት በማሰባሰብና የእውቀት ማዕከል በመሆን ድጋፍ የሚያደርግ እንደሚሆን ተገልጿል።
የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ትኩረትም በትግራይ ወራሪ ኃይል የተጎዱ አካባቢዎችን ማዕከል በማድረግ የሚሠራ ሲሆን፥ በሚኖረው የአፈጻጸም ግምገማ መሰረት ከአምስት ዓመት በኋላ ሊፈርስ ወይም ሊቀጥል የሚችል እንደሆነ ምክር ቤቱ መወሰኑን አሚኮ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version