Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሸባሪው ህወሓት በኪልበቲ ረሱ ዞን በንጹሃን ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ የሚቃወም ሰልፍ በሰመራ-ሎግያ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰመራ-ሎግያ ከተማ ነዋሪዎች አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል “ኪልበቲ ረሱ” ዞን እየፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።

ነዋሪዎቹ ቡድኑ በኪልበቲ ረሱ ዞን በሕጻናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች ላይ እየፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በማውገዝ ነው ሰላማዊ ህዝባዊ ሰልፍ እያካሄዱ የሚገኙት፡፡

ሰልፈኞቹ ” ጁንታው የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠላት ነው ፤ አሸባሪው በሕጻናት፣ሴቶችና አዛውንቶች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍና ግድያ በጽኑ እናወግዛለን፣ አሸባሪው በንጹሀን ዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን እኩይ ተግባር በፍጥነት ሊያቆም ይገባል ፤ አሸባሪው ህወሓት ታሪካዊ የአፋር ህዝብ ጠላት ነው” የሚሉና መሰል መፈክሮችን በማሰማት የወራሪውን የህወሓት ቡድን እያወገዙ እንደሚገኙ የዘገበው ኢዜአ ነው።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version