አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “መመረጥ – ተለውጦ አገርን መለወጥ!” በሚል መሪ ቃል የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅድመ ጉባዔ የአመራር መለየት፣ ማብቃትና የማጥራት ክልላዊ መድረክ ማካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
መድረኩ በአመራር ሂደት ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከርና በደካማ ጎን የታዩ ችግሮችን በመለየት የጉባኤ ቅድመ ዝግጅት ፣ የአመራር ማብቃትና ማጥራት ላይ ትኩረት አድርጎ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

