አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ በክልል ከፍተኛ አመራር ደረጃ የአመራር ግንባታ መድረክ ሀዋሳ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።
የመድረኩን ዋና ዓላማና ትኩረትን በማስመልከት ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽኅፈት ቤት ኃላፊ አብርሃም ማርሻሎ፥ የምክክር መድረኩ መሪ ቃልና ዋና የሃሳቡ ማጠንጠኛ የሚሆነው “መመረጥ – ተለውጦ ሀገርን ለመለወጥ ” ነው በሚል በተዘጋጀ ሰነድ ላይ እንደሆነ አንስተዋል።
የብልጽግና ጉዟችን ያማረ እና የሰመረ ሆኖ እንዲቀጥል አመራራችንን በብልፅግና አመለካከትና አስተሳሰብ ወደ አንድነት በማምጣትና የተግባር አንድነት በሚፈጥር መልኩ የአመራር ስምሪትንም በማጥራት ሃገራዊና ክልላዊ የብልፅግና ጉዞአችንን መንገድ መጥረግን ዓላማ አድርጎ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
ለህዝባችን በሚፈለገው ልክ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እና ተለውጦ ሀገርን የሚለውጥ አመራር እና አባላትን ማፍራት ተገቢ እንደሆነ የሚያምን የብልፅግና አመራር መፍጠር የመድረኩ ቁልፍ ተግባር መሆኑንም አንስተዋል።
ኃላፊው አሁን በተጀመረው የአመራር ግንባታ አካሄድ ፓርቲው ብቁ አመራር እየገነባ የጠራ አስተሳሰብ ይዞ እንደሚወጣ እንደሚደረግም መግለፃቸውን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ፓርቲው በምርጫ ያገኘው እድል እንጂ ድል አይደለም ያሉት ኃላፊው ይህንን ዕድል ህዝባችንን በታማኝነትና በቅንነት በማገልገል የህዝባችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥና ይህንን ተልእኮ መሸከም የሚችል የአመራር ቁመና መፍጠር ይገባናል ብለዋል።
አሁን ላይ የገጠሙንን የውስጥና የውጭ ፈተና ተጋፍጠን መልክ ለማስያዝ እያደረግን ያለነውን የሀገር ህልውና የማስቀጠል ዘመቻ ከማሳካት ጎን ለጎን በኢኮኖሚና በማህበራዊ ልማት ብልፅግናችንን ለማረጋገጥ መትጋትና ይህንን በአመራር የተግባር ጥንካሬና በፓርቲ የአሰራርና ስነ ምግባር እይታ ቅኝት በማድረግ የሁሉም አመራሮቻችን ጥንካሬ እንዲገነባና ሳንካ የሚሆኑ ጉዳዮች ደግሞ የሚታረሙበት የምክክር መድረክ ነው ሲሉም ገልፀዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

