Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ከተመድ የፕሮጀክት አገልግሎት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተደድር ሙስጠፌ መሀመድ በተባበሩት መንግስታት የፕሮጀክት አገልግሎት ቢሮ ዋና ዳይሬክተርና የአፍሪካ ህብረት ተወካይ ወርቅነሽ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው በክልሉ በተከሰተው የድርቅ ሁኔታ ዙሪያ አነጋገሩ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ስለተከሰተው ድርቅ እና የድርቁ አደጋ በዜጎች ህይወት ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመከላከል የተያዙት እቅዶችና እስካሁን የተወሰዱ እርምጃዎች ላይ ገለጻ አድርገዋል።
መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት ያደነቁት በተባበሩት መንግስታት የፕሮጀክት አገልግሎት ቢሮ ዋና ዳይሬክተርና የአፍሪካ ህብረት ተወካይ ወርቅነሽ መኮንን በበኩላቸው÷ ተቋማቸው በክልሉ የተከሰተውን ድርቅ ለመታደግ የበኩላቸውን እንደሚወጡ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version