Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል የሚያደርገውን ትንኮሳ እንዲያቆም ነዋሪዎች በሰልፍ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ገቢረሱ ዞን ገዋኔ ወረዳ ነዋሪዎች አሸባሪ ቡድኑ በአፋር ክልል የሚያደርገውን ትንኮሳ እንዲያቆም የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።

ዛሬ በገዋኔ ከተማ በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በከልበቲ ረሱና አብአላ አካባቢዎች የሚያደርገውን የንፁሃን ዜጎች ግድያ እንዲያቆም ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል ።

የወረዳው የኮምዩኒኬሽን ሃላፊ አቶ ማስረሻ ሃብቴ ለፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ አሸባሪ ቡድኑ በህፃናትና አዛውንቶች ላይ እያደረገ ያለውን በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጭፍጨፋ እንዲያቆም ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል ፤ ንጹሃን ላይ እየፈጸመ ያለውን የሽብር ተግባርም አውግዘዋል ።

የገዋኔ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሞሚን አዳጎ በበኩላቸው፥ ቀደም ሲል የሽብር ቡድኑ በሚሌ ጭፍራ ግንባር የደረሰበትን ሽንፈት አሁንም ይከናነባል ነው ያሉት።

በግንባሩ በተካሄደው ጦርነት ቤተሰባቸውን ላጡና ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ነው ያነሱት።

‘’አፋር በኢትዮጵያዊነቱ አይደራደርም ፤ አስፈላጊውን መስዕዋትነት ከፍለን አሸባሪውን እናጠፋለን’’ የሚሉና ሌሎችም ተመሳሳይ መፈክሮች በሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች መንጸባረቃቸውም ተገልጿል።

በሳምራዊት የስጋት

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version