Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከንግዱ ማህበረሰብ እና ከወንድማማች ክልሎች ከ776 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ ማሰባሰቡን የሶማሌ ክልል ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ከንግዱ ማህበረሰብ እና ከወንድማማች ክልሎች ከ776 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ ማሰባሰብ መቻሉን የሶማሌ ክልል ገለፀ።

የሶማሌ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱረህማን አህመድ እንደገለጹት፥ በክልሉ በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚውል ከንግዱ ማህበረሰብ እና ከተለያዩ ወንድማማች ክልሎች የተሰበሰበ ከ776 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

ከዚህም ውስጥ የአዲስ አበባ መስተዳደር የለገሰው የ100 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው የምግብ ድጋፍን ጨምሮ 426 ሚሊየን ብር በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ማድረስ መቻሉን አቶ አብዱረህማን ያመለከቱት።

በዚህም መሰረት 200 ሚሊየን ብር የተከፋፈለ የምግብ እርዳታ፣ 100 ሚሊየን ብር በየወረዳዎቹ የተሰራጨ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ 66 ሚሊየን ብር የተዘረጉ የውሃ መስመሮችን ለመስራትና ለማደስ ለኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ግዢ፣ 50 ሚሊየን ብር ለአደጋው ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጨማሪ ገንቢ ምግብ አቅርቦት እና 30 ሚሊየን ብር ለጋማ ከብቶች መኖ ግዢ መዋሉን አመልክተዋል።

በ6 ሚሊየን ብር በምእራብ ሲቲ ዞን ለሚገኙ ስደተኞች የተደረገ የተለያዩ ድጋፎች መደረጋቸውንም ነው የገለፁት።

ድርቁ በህይወት እና በህብረተቡ ኑሮ ላይ የሚያመጣውን ጉዳት ለመከላከል የሚያስፈልገው ተጨማሪ ርብርብ ከፍተኛ መሆኑንም የቢሮ ኃላፊው ጠቁመው ፥ ድጋፉ እንዲቀጥል ጥሪ ማድረጋቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version