Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለመገናኛ ኮሙዩኒዩኬሽን መሣሪያዎች የማርጋግጫ ሰርተፍኬት ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ ለመዘገባቸው የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂ መሣሪያዎች የባለቤትነት ማርጋግጫ ሰርተፍኬት ከሚቀጥለው ሳምት ጀምሮ እንደሚሰጥ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህነንት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) አስታወቀ።
ኤጀንሲው በተሰጠዉ ሥልጣን እና ኃላፊነት መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂ መሣሪያዎችን መጠን እና ዓይነት ለማወቅ ከዚህ ቀደም ምዝገባ ማድረጉ ይታወቃል።
በዚህም በወቅቱ ከ25 ሺህ በላይ የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂ መሣሪያዎችን መመዝገብ መቻሉን በኤጀንሲዉ የቴክኖሎጂ እቃዎች ክትትል እና ውል ዝግጅት ቡድን መሪ አቶ ተመስገን አስማረ ተናግረዋል።
የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂ መሣሪያዎችን በዓይነት እና በመጠን ለይቶ ማወቅ እንዲሁም በህጋዊ መንገድ ለተመዘገቡ መሣሪያዎች ኮድ በመስጠት ቁጥጥር እና ክትትል ማድረግ የሀገር ደህንነት ስጋቶችን ለመቀነስ እንደሚያግዝ ነው ቡድን መሪው የገለጹት፡፡
በሌላ በኩል ኤጀንሲው የባለቤትነት ማርጋግጫ ሰርተፍኬት መስጠቱ በድብቅ ወደ ሀገር ውስጥ የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂ መሣሪያዎችን በማስገባት በሚጠቀሙ ህገወጥ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚያስችለው ተናግረዋል።
ኤጀንሲው ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የባለቤትነት ማርጋግጫ ሰርተፍኬት የመስጠት መርሀ ግብር እንደሚያከናውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version