አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ64 ሺህ በላይ ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ የጫነቸው መርከብ ዛሬ ጠዋት ጅቡቲ ወደብ ገብታለች ።
ድራፍትዚላ የተባለቸው ግዙፍ መርከብ ለ2014/15 የምርት ዘመን ወደ ሀገር ውስጥ ከሚገባው የአፈር ማዳበሪያ የመጀመሪያውን 64 ሺህ 670 ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ከሞሮኮ ጆርፍ ላስፈር ወደብ ጭና የመጣች ሲሆን፥ ዛሬ ጠዋት ጅቡቲ ወደብ ገብታ የማራገፍ ስራዋን እያከናወነች ነው፡፡
ኢባትሎአድ የማጓጓዝ ስራውን በበቂ ዝግጅት በመጀመሩ መርከቧ ወደብ በገባች በሰዓታት ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ የመጫንና የማጓጓዝ ስራ በፍጥነት ማከናወን አስችሎታል፡፡
የአፈር ማደበሪያውን ከመጫኛ ወደብ ጀምሮ እስከ ሀገር ውስጥ መዳረሻዎች አጓጉዞ በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ ከባለድርሻ አካላት ጋር አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተከናውነዋል፡፡
በቀጣይ ሳምንታት ሁለት መርከቦች በተመሳሳይ ማዳበሪያ ጭነው ጅቡቲ እንደሚሰደርሱ ከኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!