Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአፈ ጉባኤ  አቶ ታገሰ ጫፎ የተመራ ልዑክ ከደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት  ሳልቫ ኪር ማያርዳት ጋር ውይይት አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ  አቶ ታገሰ ጫፎ የተመራ ልዑክ ከደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት  ሳልቫ ኪር ማያርዳት ጋር ውይይት አደረገ።

የልዑካን ቡድኑ የጋምቤላ ክልል  ርዕሰ መስተዳድርአቶ ኡመድ ኡጁሉ፣ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሳ መስተዳድር  አቶ አሻድሊ ሀሰን፥ እንዲሁም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢጋድ ሀገራት ጉዳይ ዳይሬክተር ጀኔራል አምባሳደር ፍስሀ ሻወል  እና በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲን ያካተተ ነው።

ልዑኩ በዋናነት በኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን አዋሳኝ ክልሎች አካባቢ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ዙሪያ  ላይ ተወያይቷል።

ከዚህ በተጨማሪም  በአዋሳኝ አካባቢ አልፎ አልፎ ስለሚፈፀሙ የቁም እንስሳት ዝርፊያ እና የህፃናት ጠለፋ ወንጀሎችን መከላከል ላይ የተወያየ ሲሆን፥ የመሠረተ ልማት ትስስርን በማጠናከር የድንበር አካባቢ ንግድ በሚስፋፋበት ሁኔታ ላይም መክሯል።

አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ከውይይቱ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ  ፥የሁለቱን ሀገራት እኩል ተጠቃሚነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ እንደተነጋገሩ ገልጸዋል።

ችግሮች ሲያጋጥሙም የጋራ ፎረም በማቋቋም መፍታት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች  መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version