Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኮሜሳ ዋና ፀሀፊ ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ35ኛዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የምስራቅና ደቡብዊ አፍሪካ አገራት የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ዋና ጸሀፊ ቻልሽ ካፖፕዊ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ዋና ጸሀፊዋ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የካቢኔ ጉዳዮች ዋና ሹም አምባሳደር ምህረተዓብ ሙሉጌታ አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version