Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፍሪካ ሕብረት 40ኛዉ የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ዛሬ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሕብረት 40ኛዉ የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ የሕብረቱ አባል ሀገራት ሚኒስትሮችና የአህጉሩ ልዩ ልዩ ተቋማት ሀላፊዎች በሚገኙበት ዛሬ ይጀምራል።
የምክር ቤቱ ስብሰባ “የአፍሪካ አህጉርን የስርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፣ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን ማፋጠን” በሚል የአፍሪካ ሕብረት ባዘጋጀው የ2022 መሪ ቃል ላይ ይመክራል፡፡
ጥር 28 እና 29 ቀን 2014 ዓ.ም ለሚካሄደው 35ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይም ይጠበቃል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን አባላት በመምረጥ የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ እንዲያጸድቅ የሚያደርግ ሲሆን÷ ከቀጠናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክ፣ ሌሎች የአፍሪካ ተቋማትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ጋር ያለው ትብብርና ትስስር እንዲጠናከር የማስተዋወቅ ስራ ያከናውናል።
ምክር ቤቱ በአፍሪካ ሕብረት ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትን አፈጻጸምና ሕብረቱ እ.አ.አ በ2021 ያካሄዳቸውን ስብስባዎች የተመለከቱ ሪፖርቶችን ያደምጣል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version