Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሚኒስቴሩ ከውጪ የሚገቡ የማዕድን ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት ከተመድ የቴክኒክ ድጋፍ ለማግኘት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ በኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ተወካይ ኦሬሊያ ፒ ካላብሮ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም ከውጪ የሚገቡ የማዕድን ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት በሚሰሩ ስራዎች የቴክኒክ ድጋፍ ለማግኘት እና አቅም ግንባታ ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ከብራዚል አምባሳደር ቪላሪህኖ ፔድሮሶ ጋር የብራዚል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የብረትና በማዳበሪያ ምርት ኢንቨስትመንት ላይ መሳተፍ በሚችሉበት መንገድ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ኩባንያዎቹ በአፋጣኝ ወደ ስራ የሚመገቡበትን መንገድ እንደሚያመቻቹ ማረጋገጣቸውን ኢንጂነር ታከለ ዑማ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version