Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ቦርዱ በፓርቲዎች መካከል የሚደረጉ ውይይቶች የሚመሩበት መመሪያ ሰነድን አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በ2011 ዓ.ም አፅድቀውት የነበረውን የመወያያ መመሪያ ሰነድ ማሻሻያ በማድረግ ሰፊ ውይይት ካደረጉበት በኋላ በድጋሚ እንዲፀድቅ አድርገዋል፡፡

መመሪያ ሰነዱ፥ በፓርቲዎች መካከል የሚደረግን ውይይት በስነ ምግባር የታገዘ እንዲሆን እና አስፈላጊ ከሆነው ፉክክር ውጪ የሚታየውን ያለመተማመን ለማስወገድ እንደሚረዳም ተገልጿል፡፡

ይህ መመሪያ ሰነድ ዳግም ማሻሻያ እንዲደረግበት የተፈለገበት ምክንያትም አዳዲስ ነገሮች መከሰታቸው እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡

21 አንቀፆችን ይዞ በርካታ ሃሳቦች የተካተቱበት የፓርቲዎቹ መመሪያ ሰነድ በቀጣይ በሚኖሩ ውይይቶች ላይ ስነ ምግባራዊ አካሄዶች እንዲኖሩ እና ሰጥቶ መቀበልን መርህ ያደረጉ የሀሳብ ፍጭቶች እንዲፈጠሩ ለማድረግ ፋይዳው የጎላ እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡

ይህ ተሻሽሎ የፀደቀው መመሪያ ሰነድ ከፀደቀበት ጥር 25 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያደርጉት ውይይት እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ የፀና እንደሚሆንም ታውቋል፡፡

እንዲሁም ጥር 2 ቀን 2011 ዓ.ም በፖለቲካ ፓርቲዎች የፀደቀውና በስራ ላይ የነበረው በተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረገው ውይይት የሚመራበት ስርዓትና ደንብ ሙሉ ለሙሉ በዚህ መመሪያ መተካቱም ተገልጿል፡፡

በታሪኩ ለገሰ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version