አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተፈጥሮና በሰብዓዊ ሀብት የታደለችው አፍሪካ ለዜጓቿ ምቹ እንድትሆን የአባል ሀገራቱን የእኮኖሚ ነጻነት ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ምሁራን ተናገሩ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶክተር መሳይ ሙሉጌታ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ ዶክተር መላኩ ተገኝ÷ አህጉሪቱ ለሌሎች አህጉራት የሚተርፍ ሀብት ይዛ ዜጓቿ ግን አሁንም በድርቅእና በረሃብ ይሰቃያሉ ብለዋል፡፡
እንዲሁም የጥሬ እቃ አቅራቢ ብቻ በመሆን የኢኮኖሚ ነፃነታችንን ሳናውቅና ሳናስከብር ቆይተናል ነው ያሉት፡፡
ከዚህ ችግር ለመውጣትና በኢኮኖሚ ራስን ለመቻል የአፍሪካ ሃገራት የእርስ በርስ ግንኑነታቸው ሊዳብር ይገባል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ሀብት የታደለችው አፍሪካ ለዜጓቿ ምቹ እንድትሆን የአህጉሪቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ነፃነታቸውን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ምሁራኑ ተናግረዋል፡፡
ከመደነቃቀፍ ወጥተንና አንዱ ለሌላው ችግር ከመሆን ወጥተን በጋራ ከሰራን ሀብቶቻችንን መጠቀም ያስችለናል ነው ያሉት፡፡
በተደጋጋሚ የህብረቱን ጉባኤ የምታስተናግደው ኢትዮጵያ በልማት ያላትን ተሞክሮ በዚህ አጋጣሚ ለህብረቱ አባል ሀገራት ማጋራት ይጠበቅባታል የሚል ሀሳብም አቅርበዋል ምሁራኑ፡፡
በአዳነች አበበ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

